Medrek News Conference Prof Beyene Petros

ከፖለቲካ ትርፍ ይልቅ ለሀገራዊና ህዝባዊ ጥቅሞች ቅድሚያ ይሰጥ! ከመድረክ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

ሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጥሮና በሠው/በመንግስት/ሰራሽ ፈርጀ ብዙ ችግሮች ስትናጥ ቆይታለች፣ አሁንም እየተናጠች ትገኛለች፡፡ ችግሮቹን ለመፍታት በየጊዜው በነበሩት አምባገነን መንግስታት የተወሰዱት እርምጃዎች መንግስታቱንና ጥቅሞቻቸውን ማዕከል ያደረጉ እንጂ የሀገሪቱንና የህዝቡን ችግር በመፍታት ላይ ያነጣጠሩ ስላልነበር ለህዝቡ ሲያስገኙ የነበሩት ውጤቶች አነስተኛ እንደነበሩ እንገነዘባለን፡፡ ከዚህም የተነሳ ችግሮች በችግሮች ላይ እየተደራረቡ የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ ምስቅልቅል እያወጡና እያወሳሰቡ ዛሬ ላይ […]

ESDP Older FB Page Banner Pic

በሰፈራ መርሀ-ግብር አማካይነት መንግሥት ከአንዱ አከባቢ ወደ ሌላ አከባቢ ወስዶ ላሰፈራቸው ዜጎቻችን_ደህንነት_አስተማማኝ_ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል!!!

ከኢትዮጵያ_ሶሻል_ዴሞክራቲክ (ማህበራዊ ፍትህ) #ፓርቲ (ኢሶዴፓ) የተሰጠ መግለጫ በኢትዮጵያ ውስጥ በድርቅ ከተጎዱ ወይም የመሬት ጥበት ካለባቸው አከባቢዎች ዜጎችን ወደ ለም እና ሰፊ መሬት ወዳለባቸው አከባቢዎች በይፋ ማስፈር የተጀመረው ከፊውዳሉ ሥርዓት ጀምሮ እንደሆነ ይታወቃል:: ይህ ዜጎችን ለረዥም ዓመታት ከቅድመ- አያቶቻቸው ጀምሮ ሲኖሩ ከነበሩበት ቀዬአቸው አስነስተው እንግዳ ወደ ሆነ አከባቢ የማስፈሩ ተግባር ብዙ ጉድለቶች የነበሩበት ሆኖ የቆየ ነው፡፡ከጉድለቶቹም […]

በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የኢሶዴፓ መግለጫ

በሀገራችን የተጀመረው የለውጥ ሂደት ስኬታማና ቀጣይነት ያለው እንዲሆን በብሔራዊ መግባባትና በሕጋዊና በተቋማዊ ማሻሸያዎች ላይ ሊመሠረት ይገባል፡፡ (ከኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ) የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለረጅም ዓመታት እየተፈራረቁ የገዙዋቸው ፊውዳላዊና አምባገነን ገዥዎች በጫኑባቸው አስከፊ ሥርዓቶች ምክንያት በጋራ የሚፈልጉትን በእኩልነት ላይ የተመሠረተ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ አንድነትና የበለጸገች የጋራ ሀገር መገንባት ሳይችሉ ቆይተዋል፡፡ በተለይ ባለፉት 27 ዓመታት ሀገራችንን ሲገዛ […]

Welcome to Ethiopia Sign

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ እንኳን ለሚትወዱዋት ሀገራችሁና ለሰላማዊ ትግሉ አበቃችሁ ይላል

በውጭ ሀገር በስደት ፖለቲካና በትጥቅ ትግል ተሰማርተው የቆዩ ወገኖቻችንን ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በደስታ ከመቀበል ባሻገር በሀገራችን የኃይልና የስደት ፖለቲካ ለዘለቄታው እንዲያበቃ ከልብ መሥራት ይኖርብናል፡፡ (ከኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ) አምባገነናዊ ፖሊሲዎችን የሚከተሉ አገዛዞች ባሉባቸው ሀገሮች ከገዥዎቹ የተለየ አማራጭ ሀሳብ ያላቸው ዜጎች ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው ዕድገትና ብልጽግና እንዲሁም ለፍትሐዊ የአስተዳደር ሥርዓት ያላቸውን አማራጭ ሀሳቦች በሰላማዊ አግባብ […]