Prof. Beyene Petros Interview 1

የዜጎችን መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ማስከበር የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር መሆኑ እየተዘነጋ ስለሆነ ባስቸኳይ መቆም አለበት!!

(ከኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) የተሰጠ መግለጫ )

መጋቢት —–2011 ዓ.ም                           አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለብዙ ዘመናት የኖረች ሀገር ናት፣ ሕዝቦቿም ክፉና ደጉን በጋራ ያሳለፉ፣ ትላንት የነበሩ፣ ወደፊትም የሚኖሩ ናቸው፡፡  ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ለማመን እጅግ በሚያዳግት ደረጃ የዜጐች ሕገ-መንግሥታዊ መብቶች በመንግሥት ባለስልጣኖች ሲጣሱና ማንም የጐበዝ አለቃ ራሱን ከሕግ በላይ አድርጐ ሕዝቡን ሲያስፈራራና ሲዝትበት፣ መግሥት እያየ ዝም ማለቱ በእጅጉ የሚያስገርም በሆነበት ወቅት ላይ መገኘታችን ኢሶዴፓን ከምን ጊዜውም በላይ አሳስቦታል።

  1. እጅግ በርካታ የዜጎች መፈናቀል  ባለበት ሁኔታ፣ ለምሳሌ:- ጌዲኦ፣ ኦሮሞ – ከሶማሌ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ማረቆ፣ መስቃን፣ ቅማንት፣ ሼኮ፣ ወዘተ የመሳሰሉት በኃይል እየተፈናቀሉና እየሞቱ ባሉበት – በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች መሠረት እንኳ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አለመኖሩ ፤  መንግሥት የተፈናቀሉትን ዜጎች ወደመኖሪያ ቀዬአቸውና ቤቶቻቸው ለመመለስ ከመሞከር ይልቅ  ወደ ብሔር ይዞታቸው \”የጎሣ ግዛታቸው\” መልሶ ለማቋቋም በሚያደርገው ትግል ተወላጆች ለኢኮኖሚ እና ለሥነ-ልቦና ችግር ተጋልጠዋል፡፡  ለምሳሌ: ከሶማሌ ክልል ውስጥ ኦሮሞዎችን ለማስለቀቅና በአዲስ አበባ ክልል ለማስፈር የተደረገው ሙከራ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ ይህ ሁሉም ዜጎች የመኖሪያ ቦታቸውን እንዲመርጡና በህይወት እንዲኖሩ የሚያደርጉትን ሕገ-መንግስታዊ መብቶች ይጥሳል፡፡ – አንቀጽ 32 (1)
  2. ህገ-ወጥ በሆነ የመኖሪያ ቤቶች ውድመት በ100ዎች እና 1000ዎች የሚቆጠሩ ቤት አልባ ዜጎችን መፍጠር፡- ለገዥ ህጎች አክብሮት የጎደለው እና በዜጎች  ላይ በተወሰደው ኢሰብዓዊ ጭካኔ የዜጎች የባለቤትነት መብት መጣሱ በቅርቡ በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን የአስተዳደር/የሥርዓት ንቅዘት ያሳያል፡፡ (ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 40). በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ለጋጣፎ ከተማ የዜጎችን መኖሪያ ቤቶች በድንገት በማፍረስ እንዲፈናቀሉ መደረጋቸውና ሕጻናትና መጫት እናቶች ጭምር እላያቸው ላይ ቤት ስለመፍረሱ ሰምተን እጅግ አሳዝኖና፣ አሳፍሮናልም፡፡  መንግሥት የዜጎቹን መሠረታዊ የቤት ችግር ለማስወገድ ባልቻለበት ሁኔታ ዜጎች በግል ጥሪት የሰሩትን ቤት ያለ ዕቅድና ምትክ መጠለያ ሳይዘጋጅላቸው በድንገት ለዘመናት የኖሩበትን ቤት አፍርሶ ሜዳ ላይ መጣል የዜግነት ክብር የሚነካ ድርጊት ከመሆኑም በላይ የወደመው የዜጎች ሀብት ማለት የሀገር ሀብት መሆኑን በቂ ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ ተግባር ነው ፡፡
  3. በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ በኮዬ ፈጬ፣ ዜጎች ለዓመታት ባጠራቀሙት ገንዘብ የኮንዶሚኒየም ቤት ዕጣ ደርሶአቸው እንዳያገኙ መደረጋቸው የህግ የበላይነት መከበር ጥያቄ ያስነሳ ድርጊት ሆኗል፡፡በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ፍቃድና የመኖሪያ ቤት አፓርታማዎችን ለትክክለኛዎቹ ባለቤቶች ለማስተላለፍ በሚደረገው ሂደት ለተፈጠረው ጥልና ጣልቃ ገብነት  ምክንያት የሆነው የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት፣ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ስምምነት ላይ ሳይደረስና ከሕግ አግባብ ውጭ ሠርቶ ከሆነ፣ ሕንፃውን ለመገንባት ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ባለመቻሉ ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለበት፡፡  እናም የእነዚህ ዜጎች መብቶች በፖለቲካ ግርዶሽ እና ፍጆታ ምክንያት መጣስ የለባቸውም፡፡  በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት/አስተዳደር መካከል የክልል ደንቦች ጥሰት በመጥቀስ ችግሩን ለመቅረፍ በሐቅ ያልተሳካው በመንግሥት የአካሄድ ችግር ነው፡፡

ህገ-መንግስታዊ ባልሆኑ ህዝባዊ አመራሮች እና ቡድኖች፡- ለምሳሌ: በአንቀጽ 49 (5) በግልጽ እንደተቀመጠው በአዲስ አበባ የባለቤትነት መብት ጉዳይ አለመግባባት ሊፈጠር አይችልም፡፡ በኦሮሞ ክልል ማዕከላዊ ቦታውን መጥቀስ እና በአገልግሎቶች እና አቅርቦቶች ተደራሽነት በሁለቱ መካከል ማቀናጀት አስፈላጊ እንደሆነ ቢታወቅም በፌዴራል መንግሥት ሥልጣን አዲስ አበባ ክልል 14  ሆኖ በመካለሉ እውቅና ያለውና በሽግግር መንግስት ስምምነት ላይ የደረሰበት ነው፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁሉም ፖለቲካ በወቅቱ ሕገ-መንግስታዊ ድንጋጌዎች መሠረት መጫወት ይኖርበታል፡፡  ከዚህ ውጭ ማሰብ እና መጥቀስ ስንሞክር ሐቀኛ ​​አለመሆን እና ለራስ አለመታመንን ያስከትላል!

ስለሆነም የአዲስ አበባ ጉዳይ በሕገ-መንግስቱ ድንጋጌ መሠረት መታየት ያለበት ጉዳይ እንደመሆኑ፣ ተገቢ ያልሆኑ ጥያቄዎች እየተቀሰቀሱ የሕዝባችንን ሰላማዊ ኑሮ እንዳያውኩ፣ መንግስት ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ኢሶዴፓ ያሳስባል፡፡

በሌላ በኩል በህወሃት የበላይነት የሚመራ የኢህአዴግ መንግሥት ተጽዕኖ ቀርቷል እየተባለ ቢነገርም፤ አሻራው ያልጠፋ በመሆኑ ግጭቶች እዚህም እዚያም ሲከሰቱ ታይቷል፡፡ እየታዩም ናቸው፡፡ ለአብነት ያህል በውጭ ሀገር በስደት የኖሩ ፓርቲ መሪዎች ወደ ሀገር ቤት መመለስን ተከትሎ በተደረጉ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ወቅት ተይዘው በወጡት ኢ-ሕገ መንግሥታዊ በተባሉ ባንድራዎች ሳቢያ በብዙ ቦታዎች በተፈጠሩ ግጭቶች የተገደሉና ቤት ንብሬታቸው የወደመባቸው ዜጎች አሉ፡፡ ከሃይማኖት ልዩነት ጋር በተያያዘም ፅንፈኛ ሀይሎች በሃላባ አብያተ ክርስቲያናት ፣በወሎና ጎንደር ደግሞ መስግዶችን በማቃጠል ሀገርና ሕዝብ እንዳይረጋጋ ስጋት ፈጥረዋል፡፡

ስለሆነም፣ መንግስት በሚከተሉት አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ አስቸኳይ ሕጋዊ  እርምጃ እንዲወስድ ኢሶዴፓ በአፅንኦት ያሳስባል፥

  1. የአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ በሕገ-መንግሥቱ ድንጋጌ መሠረት መታየት ያለበት እንደመሆኑ፣ በነዋሪዎቿ ላይ ያለመረጋጋት፣ ፍርሃትና ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ከአፍራሽ እንቅስቃሴያቸው እንዲቆጠቡ በማድረግ መንግሥት የህግ የበላይነት የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ፡፡  
  2. መንግሥት የተፈናቀሉትን ዜጎችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ ሲገባው፣  በብሔራቸውና በጎሣ አሰላለፍ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማሕበራዊ ሁኔታዎች ሙሉ ለሙሉ እንግዳ በሆኑ አካባቢዎች ማለማስፈር መሞከሩን ማቆም አለበት፡፡
  3. መንግሥት ለዜጎች መጠለያ ለማቅረብ ባለበት ግዴታው፡-  ከየቦታው ለተፈናቀሉና ለሚፈናቀሉ አነስተኛ ገቢም ሆነ ገቢ   ለሌላቸው ዜጎች መኖሪያ ቤት ማዘጋጀት አለበት፣
  4. ለከተማ ነዋሪ ዜጐች የመኖሪያ ቤቶች በማዘጋጀት ሰበብ ከሕግ አግባብ ውጭ     የተፈናቀሉት አርሶ አደሮች ባስቸኳይ ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፈላቸው ።

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ

                     መጋቢት —–2011 ዓ.ም                           አዲስ አበባ

Posted in Press Releases.

One Comment

  1. Pro,our father we are proud on you please continue your fighting aganist the …….

Comments are closed.